ረቡዕ 24 ኤፕሪል 2013

US-BACKED EGYPT MILITARY “TO CONTROL NILE” | ISRAELI MEDIA

Egypt’s military, financed by the United States, has been preparing for what could be a war for control of the Nile.
Western intelligence sources said the military command has urged President Mohammed Morsi for a buildup meant to block any attempt to divert the Nile. They said the military envisioned a crisis with Ethiopia that could threaten water supplies to Egypt and Sudan.Ethiopia Egypt Nile river map
“For the Egyptian military and government, this is perhaps the most burning security issue today,” a source said.
The sources said Morsi has sought to form a military alliance with Sudan to prevent Ethiopia from constructing a dam along the Nile. The Renaissance Dam was meant to draw 84 billion cubic meters of water from the Nile, sufficient for hydroelectric power.
“The military has been preparing for the prospect that air strikes would be ordered to stop construction or simply destroy the Ethiopian dam,” the source said.
Egypt, which receives 60 percent of the river’s water, has insisted on preferential rights to the Nile. The sources said the Morsi regime was expected to issue a stark warning to Addis Ababa during its next session of the Egyptian-Sudanese-Ethiopian technical committee in late May 2013. The Nile is shared by 10 countries.
“Certain measures have to be followed to make sure that Ethiopia gets the water necessary for storage in the dam in line with Egypt’s consent and needs,” an Egyptian official told the state-owned Al Ahram daily on April 18.
The sources said Egyptian military planning was based on the delivery of the new F-16 Block 52 multi-role fighter from the United States. They said the Egyptian Air Force, expected to receive 20 such aircraft in 2013, has determined that the latest F-16 variant, which included extended fuel tanks, would enable an attack on the Ethiopian dam.
Egypt has determined that the Renaissance Dam would comprise a loss of between eight and 18 million cubic meters per year. The sources said Cairo has repeatedly warned the United States of the danger of the Ethiopian project.
“The U.S. input here is crucial, because its aircraft would be used for any military operation against Ethiopia,” the source said.
***********
Acknowledgements to AmharicTube.com who bought the news from MiddlesEast Newsline for $8 USD. Originally titled “Egypt Military Gears For Water War“.

ቅዳሜ 6 ኤፕሪል 2013

100 People Who Changed the World

This is a list of 100 people who have changed the world.

People Who Changed the World

# 95 Emperor H/selasse  but Ethiopia doesn't respect this leader

To check follow;   http://www.biographyonline.net/people/people-who-changed-world.html

christ 1. Jesus Christ (c.5BC - 30AD) Spiritual Teacher, central figure of Christianity.
christ 2. Thomas Jefferson (1743- 1826) 3rd President of US. Principle author of Declaration of Independence
christ 3. Mikhail Gorbachev (1931 - ) Leader of Soviet Union. Oversaw transition from Communism in Eastern Europe.
christ 4. Martin Luther King (1929 - 1968) Non-violent civil rights leader
christ 5. Nelson Mandela (1918 - ) Anti-apartheid leader. First President of democratic South Africa in 1994.
christ 6. Lord Buddha (c 563 - 483BC) Spiritual Teacher and founder of Buddhism.
christ 7. Winston Churchill (1874 - 1965) Prime Minister of Great Britain during Second World War.
christ 8. William Shakespeare (1564- 1616) English poet and playwright.
christ 9. Adolf Hitler (1889 - 1945) Dictator of Nazi Germany.
christ 10. Abraham Lincoln (1809 – 1865) President of US during civil war, helped end slavery.

የቀበጡ እለት ሞት አይገኝም ከቴዲ አፍሮ ወደ ቅዱስ ገብሬል (መልካምሰው አባተ)

ከአመታት በፊት አንድ ቀን በጣም አንቀለቀለኝ፡፡ ጠገብኩ፡፡ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮን በመተቼት ጋዜጣ ላይ ፃፍኩ፡፡
ከአድናቂ ጋር የሚያጣላ ነገር እንዳልጻፈ ሰው በነጻነት በሰፈሬ እዞር ነበር፡፡ ደፋር እኮ ነኝ፡፡ ቴዲ አፍሮን
የሚያክል ‘ጣኦት’ ተችቶ በነፃነት መዞር? የእንጦጦን ነፋስ ለመቀበል ከአዲሱ ገበያ ተነስቼ ወደ ላይ
እንጎራደዳለሁ፤ በኩራት፡፡ የቴዲ አፍሮን ምስል የለበሱ አምስት ወጠምሻ ወጣቶች ተጠጉኝ፡፡ መጀመሪያ አልፈራሁም፡፡
ዙሪያዬን በአምስት ጎረምሳ ስታጠር ግን ተንቦቀቦኩ፡፡ አንገቴ ስር ጫማ ጥፊ ገብቶልኝ ከመውደቄ በፊት አንድ ዙር
አማተርኩ፡፡ ዙሪያዬን ከበውኛል፡፡ አጠር ቀጠን ያለውን አድናቂ ገፍትሬው ወደ ሰሜን ሸመጠጥኩ፡፡ ተከተሉኝ፡፡
ስንሮጥ እንጦጦ ደረስን፡፡ የጎጃምን መስመር ይዤ እፈተለክ ቀጠልኩ፡፡ እንዲህ እንደምሮጥ አላውቅም ነበር፡፡ ‹‹ሩጫ
ለነ ቀነኒሳ ብቻ የተሰጠ ፀጋ ይመስለኝ ነበር፡፡›› ስል እያሰብኩ እሮጣለሁ፡፡ አባራሪዎቼም ይከተሉኛል፡፡ የዋዛ
አድናቂዎች አልነበሩም፡፡
‹‹ምን ያህል ቢያደንቁት ነው? ወይኔ ሰውዬው! ትምህርት ትቼ ብዘፍን ኖሮ ልቡ እስክትፈርጥ ድረስ የሚሮጥልኝ
አድናቂ ይኖረኝ ነበር፡፡ አባቴ ግን ሸወደኝ፡፡ ተማር ተማር እያለ የብርም የአድናቂም ድሃ አደረገኝ፡፡ ወደትምህርት
ቤት ሂድ ከሚለኝ እንደ አቶ አፍሮ ወደ አገር ቤት እያልክ ዝፈን ቢለኝ ምን ነበረበት?›› ስል እየተቆጨኹ
እሮጣለሁ፡፡ ሩጫ ከቁጭት ጋር አይሄድም፤ ያደክማል፡፡  ….ብቻ እንደ ቀነኒሳ ኋላዬን ገልመጥ እያልኩ እያየሁ እሮጣለሁ፡፡
ሱሉልታን አለፍኩ፡፡ አቤት ዳገቱ፡፡ ሮጥኩ፡፡ ሮጥኩ፡፡ ሮጥኩ፡፡ ሰላሌ ሜዳ ላይ ስደርስ ሩጫዬን ጨረስኩ፡፡ ሰው
እንዴት ዳገቱን አልፎ ሜዳው ላይ ሲደርስ ሩጫውን ይገታል? ተስፋ ቆረጥኩ፡፡ ተስፋ በቆረጠ ሁናቴ ወደ ኋላ ዞር ብዬ
ሳማትር አባራሪዎቼም ሩጫቸውን ጨርሰው ኖሯል፡፡ ተመስጌን አልኩ፡፡ አንደኛው ብቻ ተስፋ በመቁረጥና ተስፋ በማድረግ
መካከል ሆኖ ልሩጥ ልተወው እያለ በጥቂት ሜትሮች ከእኔ ኋላ ቆሟል፡፡ ትንሽ ቢሮጥ እኔ ነዳጅ ስላልነበረኝ ሊይዘኝ
ይችል ነበር፡፡ እግዚሃር ይስጠው መሮጡን ትቶ መሳደብ ጀመረ፡፡ ‹‹ቆይ ጠብቅ አንተ ውሻ! አንተ ነህ ቴዲዬን
የምትሳደበው? ሽንታም! ፈሳም! በቀቀን!…..፡፡ ስማ ደግሞ በዛው ንካው ወዳገርህ ወደ በጌ ምድር፡፡ በግ የበግ
ልጅ እንዲሁም የፍየል፡፡ ገበሬ ነህና ወደ ግብርና ትመለሳለህ እንጅ አዲሳባን ዳግም አትረግጣትም፡፡……›› አለና
ግራ ኋላ ዞሮ ተመለሰ፡፡ እኔም መንገድ ዳር ቆሜ ከበጌ ምድር አቅጣጫ የሚመጣ መኪና እጠብቅ ጀመር፡፡ አንድ እንጨት
የጫነ አይሱዙ ከጎጃም ሲመጣ አየሁ፡፡ ሲደርስ እጄን አውለበለብኩለት፡፡ ሾፌሩ አቆመልኝ፡፡ ‹‹ጋቢና ሙሉ ስለሆነ
ከላይ ውጣ!› አለኝ ሾፌር፡፡ ወጣሁ፡፡ አይሱዚው ትንሽ እንደሮጠ አሯሩጠውኝ ከተመለሱት አድናቂዎች ጋር ደረሰ፡፡
አባራሪዎቼ የመንገድ ዳር ይዘው ወዳገራቸው ወክ ያደርጋሉ፡፡ አይሱዚው እና እኔ አጠገባቸው ስንደርስ እጄን
አውለበለብኩላቸው፡፡ ባለማመን እና በንዴት ፊታቸው ጉበት ሲመስል ታዬኝ፡፡ ወደ አዲሳባ ቀድሜያቸው ስመለስ እኔን
የተሰማኝ ሃሴት እነሱን የተሰማቸው ንዴት ቢጋጭ 6 ሺ ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኤነርጂ ይፈጥር ነበር፡፡ አጋነንኩ
እንዴ? እሺ 60 ሺ ይሁን፡፡
አንደኛው አድናቂ አይሱዚው ላይ መሆኔንም እያዬ በሩጫም ሊከተለኝ አማረው፡፡ ሮጠ፡፡ ቆይቶ ሲያስበው መኪና ላይ ነው
ያለሁት፡፡ ሩጫውን አቆመ፡፡ ቢሮጥ ፈልጌ ነበር፡፡ ምናልባትም ፈጣን ሯጭ ሆኖ አይሱዚውን ሊደርስበት ይችል ይሆን
ነበር፡፡ ይህም ማለት አገሬ የ800 ሜትር ሯጭ አገኘች ማለት ይሆን ነበር፡፡ ከአድናቂነት ወደ ተደናቂነትም
ይሸጋገር ነበር፡፡ ለጀግና በመዝፈን ጀግንነቱን ያስመሰከረው እና አጥር ያልተበጀለት የዝና ኢምፓዬር የመሰረተው ቴዲ
አፍሮም ይዘፍንለት ነበር፡፡
*
*****                           *
በሌላ አንድ ቀን ማለትም በቀደም አራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ቁጭ ብዬ ሻይ እየጠጣሁ የቀጠረኝን ጓደኛዬን
እጠብቃለሁ፡፡ አንድ የራሱን ምስል በቲሸርት አሳትሞ የለበሰ ወጣት ወደ እኔ መጣ፡፡ ሰላም አለኝ፡፡ ሰላም
አልሁት፡፡ ተሰላለምን፡፡
‹‹አስታወስከኝ?›› አለ፡፡
‹‹ãረ በፍፁም!››
‹‹አንዴ ቴዲ አፍሮን በጋዜጣ ተችተኸው ከጓደኞቼ ጋር ልንደበድብህ ስናባርርህ ነበር፡፡ ትዝ አለህ?››
‹‹አሃ፤ ትዝ አለኝ፡፡ እና አሁንም እንሯሯጥ እያልከኝ ነው?›› አልኩት፡፡
ሳቀ፡፡
‹‹ቁጭ በል፤ ቁጭ ብለህ አውራኝ!››
ተቀመጠ፡፡
‹‹በውነቱ ያኔ ተሳስተናል፡፡ በእኔና በጓደኞቼ ስም ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ መለስ ዜናዊ የሰጠህን የመፃፍ መብት እኛ
ልንነጥቅህ መነሳታችን መለስን ቅዱስ እኛን እርኩስ ያደርጋል፡፡ ኦባማ እንዳለው የመፃፍ መብትን በመንፈግ ከመለስ
ዜናዊ አንሶ መገኘት ማለት ደግሞ ሞት ማለት ነው!›› አለ፡፡
አባባሉ አንጀቴን በላው፡፡ ደግሞም አደነኩት፡፡ በልቤ ውስጥ የነበረችኝን ይቅርታ አንድም ሳላስቀር አውጥቼ
ሰጠሁት፡፡ ኪሴ ውስጥ ገንዘብ ቢኖረኝ ኖሮም ልስጥህ ባልኩት ነበር፡፡ በውነቱ አንድ ኢትዮጵያዊ ወጣት ከዘፋኝ
ተከታይነት ወጥቶ በራሱ ፍልስፍና እየኖረ የሶቅራጥስን የሚያክል ጥቅስ ሲናገር መስማት የደስታ ለቅሶ ያስለቅሳል፡፡
ሆኖም በወቅቱ በአዲሱ የሊዝ አዋጅ ምክንያት አጎቴ ቤቱን በተከራዩ ስለተቀማ ለቅሶ ላይ ስለነበርኩ እና እንባዬንም
ስለጨረስኩት ሳላለቅስ ቀረሁ፡፡
‹‹በጣም አመሰግናለሁ!›› አልሁት፡፡
‹‹ማመስገን ያለብኝማ እኔ ነኝ፡፡ ይገርምሃል ያኔ እስከሰላሌ ሜዳ አንተን ከማባረራችን በፊት እኔና ጓደኛቼ ወንድ
ልጅ አባረን አናውቅም ነበር፡፡ ሴት ነበር የምናባርረው፡፡ በዚህ የተነሳ ፒያሳን እንጂ ሰላሌ ሜዳን አናውቀውም
ነበር፡፡ አንተን ከማባረራችን በፊት እኔም ጓደኞቼም ከአዲስ አበባ ወጥተን አናውቅም፡፡ በተለይ እኔ ከአዲስ አበባ
ውጭ የማውቀው ሩቅ አገር ቃሊቲ ነው፡፡ ዛሬ ግን ዕድሜ ላንተ ታሪከ ተቀዬረ፡፡ ጧት እንጦጦ ብትመጣ እኔን
አታጣኝም፡፡ እንጦጦ ብታጣኝ እንኳ ሰላሌ ሜዳ ታገኘኛለህ!›› ሲል አብራራ፡፡
‹‹እንዴት?›› ስል ጠየኩ፡፡
‹‹ያኔ አንተን ሳባርር ነው እግዜር የሰጠኝ ተሰጥኦዬ ሩጫ መሆኑን ያወኩት!››
‹‹ግንኮ ሮጥክ እንጂ አልያዝከኝም?!››
‹‹ባልይዝህም ሯጭ መሆኔ ገባኝ፡፡ እናም እሮጥ ጀመር፡፡ ዛሬ በክለብ ታቅፌ ክለቤና አገሬ የሚመኩብኝ ሯጭ
ሆኛለሁ!›› አለ፡፡
በውነቱ እጅግ በጣም ደስ አለኝ፡፡ አንድ ያገሬ ልጅ እኔን ተመስሎ ተሰጥኦውን ሲያገኝ እንዴት አልደሰት፤ ለዛውም
ሩጫን የመሰለ ተሰጥኦ፡፡ ከራስ አልፎ አገር የሚያስጠራ ታላቅ ሙያ፡፡ እግዜር አንድን ሰው ሊለውጥ ሲፈልግ መልዓኩ
ገብሬልን ነው የሚልከው፡፡ አንዳንዴ ሳስበው ግን እኔንም ይልከኛል መሰል፡፡
‹‹በነገርህ ላይ ያኔ ስታሯሩጡኝ አንድ የረሳችሁት ነገር ነበር!›› አልሁት፡፡
‹‹ምን?››
‹‹እኔም እንደናንተ የቴዴ አፍሮ ዘፈኖች አድናቂ መሆኔን፡፡ ልዩነቱ እናንተ ሰውዬውን እኔ ሙዚቃውን መውደዳችን
ነው፡፡ እግዚሃር በየለቱ በሚጎበኛት አገር የሰው ጣኦት መፍጠር ጥሩ አይደለም፡፡ በጋኔን ያስመታል!›› አልኩት፡፡
‹‹እግዜር ኢትዮጵያን በየለቱ ይጎበኛታል ብለህ ታምናለህ እንዴ?››
‹‹ሌላ ምን ምርጫ ይኖረዋል፡፡ ወደ ሰሜን ቢያይ አመፀኛ፤ ወደ ደቡብ ቢቃኝ የባህር ወንበዴ፣ ወደ ምዕራብ ቢያማትር
ግብረሰዶማዊ፤ ምስራቅ ቢያቀና አላውቅህም የሚለው ትውልድ ይገጥመዋል፡፡ አንገቱን ነቅንቆ ወደኛው ይመለሳል፡፡
አያያዙን ስተነው እንጂ የዘመኑ አብርሃሞች እኛ ነበርን!›› አልኩት፡፡ የሰማኝ አልመሰለኝም፡፡
‹‹ይገርምሃል፡፡ ዘፈን ከመውደዴ የተነሳ ዘፋኝ ማምለክ ጀምሬ ነበር፡፡ ይሄ ራስን መናቅ ከእግዜር መራቅ መሆኑ
ሲሰማኝ ራሴን ጠላሁ፡፡ ተፀፀትኩ፡፡ የሩጫ ክህሎቴ ደግሞ አፅናናኝ!›› አለ፡፡
‹‹ጥሩ አድርገሃል፡፡ ያኔ ግን ብትይዙኝ ኖሮ ምን ታደርጉኝ ነበር?›› ስል ጠዬኩ፡፡
‹‹እንደ መጥምቁ ዮሃንስ አንገትህን እንቆርጠው ነበር፡፡ የሄሮድስ እርኩስ መንፈስ በዘፈን ታዝሎ አናታችን ላይ
ሰፍሮ ነበር!›› ሲል መለሰ፡፡
ዘገነነኝ፡፡ ‘’ገረፍ ገረፍ አድርገን እንለቅሃለን!” የሚል ነበር የመሰለኝ፡፡ ወይ ጉድ፤ ከሞቴ አሟሟቴ፡፡ አገሬ
በሴቶች ጉዳይ ብቻ ትጨነቃለች፡፡ እንዲህ አይነት የወንዶች ጉዳይ መኖሩን ሳታውቅ፡፡ አይ የዛሬ ልጅ፤ አባቶቹ
ለእናት አገራቸው ፈረንጂ ሲገሉ ቢያይ እሱ ለዘፈን እኔን ወንድሙን ሊገድል ተነሳ፡፡ በዚህ የተነሳ ‘’አለም ላይ
የመጀመሪያው ማህበራዊ ብርሃነ ህሊና (social enlightenment) የታዬው በኢትዮጵያ ሲሆን የመጨረሻው
ማህበራዊ ዝቅጠት (social depression) የተከሰተውም በዚችው በኢትዮጵያ ነው’’ ብለው የፃፉትን
ምዕራባውያን ፀሃፍት ላምናቸው ወሰንኩና ከአርበኝነቴ ጋር ስለማይሄድ ተውኩት፡፡ ግን በጣም ነበር የከፋኝ፡፡ እስኪ
አንባቢያን አስቡት፤ በዘፈን ሰበብ የሞት እጩ ሆኖ ከመቅረብ የባሰ ምን አስከፊ ነገር አለ?!
‹‹ብቻ ግን ገብሬልዬ ጠበቀን፡፡ ትዝ ይልህ ከሆነ ያኔ ያሯሯጥንህ በገብሬል ዕለት ነበር፡፡ ሰው ከመግደል
የዳንኩበት ሩጫ እንደምችል የተረዳሁበት ቀን ስለሆነ በየወሩ ገብሬልን እዘክራለሁ፡፡ በመጭው ገብሬል የትም
እንዳትሄድ እኔ ቤት ነህ፡፡ ዳቦ ትቆርሳለህ!›› አለ፡፡
‹‹በል በየወሩ በ19 እቤትህ አልቀርም፡፡ በውነቱ ከቴዲ አፍሮ ወደ ገብሬል ያደረከው ሽግግር ወይም ዕድገት የፎቅ
እንጂ የአስተሳሰብ ዕድገት ለማይታይባት አገራችን አስደናቂ ዕድገት ስለሆነ በታላቅ ምሳሌነቱ አገር ቢያውቀው ምን
ይመስልሃል?›› አልኩት፡፡
‹‹ጥሩ ነው፡፡ ፃፈው፡፡ ይሄን ለለውጥ የተዘጋ ህዝብ በደንብ ስደብልኝ ደ’ሞ፡፡ ምነው እንዳንተ መፃፍ በቻልኩ ልክ
ልኩን እነግረው ነበር!›› አለ፡፡
‹‹ãረ በገብሬል ይዤሃለሁ፤ ህዝብ እንደዚህ አይባልም፤ ህዝብ እኮ እግዜር ማለት ነው?!›› አልኩት ኮስተር እና
ኩምትር ብዬ፡፡
‹‹ãረ እባክህ! እሱን ብሎ እግዜር፡፡ ለነገሩ ቢሰድቡትስ ይሰማል ብለህ ነው፡፡  በፓርላማ መዶሻና እና በዘፋኝ
ማይክራፎን ደንቁሮ!››
‹‹አንተ ራስህን ከለወጥክ ይበቃል፡፡ ሌላውም እንዳንተ ሲለወጥ ባንድ ላይ አገር ይለወጣል፡፡ ሒሳቡ እንደዚህ
ነው፡፡ ከዚህ ወዲያ ራስህን እንጂ ሰው አትከተል!››
‹‹አዎ፡፡ በተለይ ዘፋኝ አልከተልም፡፡ ዘፋኝን ብትከተለው ጥሩ ቦታ ወሰደህ ቢባል  ስቱዲዮ ነው፡፡ እንደ ስቱዲዮ
የጠበበ የአለም ክፍል ደግሞ የለም፡፡ የኮንዶሚኒዬም ጠባቡ እንኳ ስቱዲዮ ይባላል፡፡……›› አለ፡፡
የመሳቅም የማውራትም ስሜት አንድ ላይ መጣብኝ፡፡ ማውራቱን አስቀደምኩ፡፡
‹‹በዚህ እንኳን አልስማማም፡፡ አንዳንዴ ከጠባቡ የስቱዲዮ አለም የሚወጡ ዘፈኖች ለአለም መፍትሄ ሲያመጡ ታይቷል፡፡
ጦርነትና ሰላም ያልፈታውን ዘፈን ፈቶት ያውቃል፡፡ ለምሳሌ የቴዲ አፍሮ ‘ኻብ ዳህላክ’ የተቆረጠ የኢትዮጵያን ብርሌ
አንገት መልሶ የሚቀጥል ይመስለኛል!›› አልኩት፡፡
‹‹………ብለን ተስፋ እናድርጋለን፡፡ ዘጠና ዘጠኝ ከመቶ ያገሬ ዘፈን ግን ከአንሶላ ውስጥ ወግ አልወጣም፡፡ የአንሶላ
ውስጥ ወግ ከኦርጋዝም ዘዴ በስተቀር ምን ይነግርሃል!? ለሱ ለሱማ እኛም አናንስም….›› አለ፡፡  በጣም ሳኩ፡፡
‹‹ወደፊት ከአንሶላ ወጥተው እንደሚዘፍኑ ተስፋ እናደርጋለን!››
‹‹ብርዱን ይችሉታል ብለህ ነው?››
‹‹ቴዲ አፍሮ ከአልጋ ወርዶ ከቤተመንግስቱ ማማ ላይ ወጥቶ በመለስ መላጣ አንዣቦ ቀጥሎም ቃሊቲ ገብቶ ብርዱ
እንደሚቻል ያሳያቸው መሰለኝ!››
‹‹አይ፤ የቃሊቲን ብርድ እንኳ እንዳልቻለው አረጋግጠናል፡፡ ቃሊቲ የፖለቲካ አቋሙን አስለወጠው እንጂ ምን ሰራለት››
‹‹በአስራ ሰባት መርፌ የጠቀመው ቁምጣ ለውጥ ካላመጣ እኔ የአቋም ለውጥ ላምጣ ብሎ እንደሆንስ?››
‹‹አይመስለኝም፡፡ ነገሩ ሌላ ነው፡፡ በቴዲ አፍሮ የፖለቲካ አቋም ውስጥ ፍቅር ፊቸሪንግ ገባኮ!››
‹‹ምንድን ነው የምታወራው?››
‹‹የቴዲ አፍሮ ጊዜያዊ የፖለቲካ አቋም ለፍተሻ ወደ ተቃዋሚ ላቦራቶሪ መውረድ አለበት፡፡ የሁለት መቶ ሺ ብር
የአልማዝ ቀለበት ለፍቅረኛው ማሰሩን ሰማህ ደ’ሞ?!››
‹‹አይ፤ ከመርካቶ የጎዳና ህፃናት ጋር ፋሲካን አብሮ ቢውል አይሻልም ነበር፤ ነፍሱንም ዝናውንም አንድ ላይ
ለማስኬድ?!››
‹‹ማን ይምከረው፡፡ ምን የዛሬ ዘፋኝ እሱ መካሪ፤ ራሱ ተመካሪ፤ ራሱ አርቲስት፤ ራሱ ሳይንቲስት፤ ራሱ ገጣሚ፤ ራሱ
ዜማ ከግጥም አጋጣሚ፤ ራሱ ኪቦርዲስት፤ ራሱ ጊታሪስት፤ ራሱ ዘፋኝ፤ ራሱ ዘማሪ፡፡ እንደ መድሃኒያለም በአንድ ጊዜ
በሁሉ ቦታ እየተገኘ ቄሳርና እየሱስን አምታታብን’ኮ፡፡…..››
‹‹ይገርማል!››
‹‹እንዳው የምሩ ግን፤ ግለሰብ ግንባታ፣ ማህበረሰብ ግንባታ እና ሙዚቃ እንደ ስላሶች የተዋሃዱ አይመስልህም፤ በዚች
ምስኪን አገራችን? የአገሬ ሰው ሙዚቃን ቅዱስ መንፈስ አድርጎ በትዝታ፣ አንቺዬና አንቺ ሆዬ ሲቆዝም ይውላል፡፡
ከእግዜር ርቆ፤ ከስራ ርቆ፤ በእውኑ ተርቦ፤ በህልሙ ቅቤ ጠጥቶ የውሸት ሲኖር ሳይ እዝናለው፤……›› አለ፡፡
‹‹እንዲህ ትፈላሰፋለህ እንዴ?››
‹‹ትንሽ እውቀት አደገኛ ስለሆነ ይሆናል የሚያፈላስፈኝ፤…..››
‹‹ትንሽ የሚባል ዕውቀት የለም፡፡ ያለችህን ባግባብ ከተጠቀምክ አንተ አዋቂ ነህ፡፡ ለምሳሌ ቴዲ አፍሮ ያለችውን
ዕውቀት በመጠቀሙ የሙዚቃውን ምህዳር በራሱ ሰሌን ጠቀለለው፡፡ ከዚህ ወዲያ ቴዲ አፍሮ በዘንድሮው አልበሙ በመዝፈን
ፋንታ ዘነጠብን ብለህ ብታወራ ምቀኛ ነህ!›› አልኩት፡፡
‹‹ዘንድሮ ቀሽም ዘፈነ እንዴ?››
‹‹የአቤል ሙሉጌታንና ሃይሌ ሩትን ዘፈን ከመስማትህ በፊት ከሰማኸው በርግጥ አሪፍ ነው፡፡ ቴዲ አፍሮ የሃይሌን
አቤልን ዘፈን ሳይሰማ አልበም ማውጣቱ ሳይጎዳው አልቀረም፡፡ ባገሪቱ የሙዚቃ ባለሙያ ከሌለ እኛው እንተንትነው
እንጂ!…..››
‹‹ወይ ጉድ፤ አንተ ነገረኛ ነህ፡፡ እስኪ እኔም እሰመዋለሁ፤….››
‹‹እስካሁን ሳትሰማው? እውነትም ጨክነሃል!››
‹‹ከቴዲ አፍሮ ዘፈን ይልቅ የቴዲ አፍሮ የ200 ሺህ ብር የጣት ቀለበት ወሬ ነው የመሰጠኝ፤…..፡፡ እስኪ አስበው
ረሃብ ጥርስና ጥፍር አውጥቶ የአዳሜና ሄዋኔን ጨጓራ ሲቧጥጥ በሚውልበት አዲሳባ፤ 200 ሺ ብር አንድ ኢንች
ዲያሜትር ቀለበት ሆኖ፤ ከአንድ አለንጋ ጣት ላይ እንደዋዛ ተሰንቅሮ ያለስራ ሲወዛዎዝ ሲውል ስታይ ፃፍ ፃፍ
አያሰኝህም?›› አለ፡፡
‹‹አንተን ሩጥ ሩጥ አሰኘህ እንዴ?›› ብዬ አሳኩት፡፡
‹‹እውነት እንደ ጋዜጠኛ ይሄ ነገር አያሳስብህም?›› አለ ቀጥሎ፡፡
‹‹በርግጥ ያሳስበኛል፡፡ አንዳንዱ የዚህ ዘመን ፍቅር እንደ ኤሌክትሪክ በማዕድን በኩል ካልሆነ ወደ ልብ አልሄድም
እያለ ችግር ሆነኮ፡፡ ቴዲዬን እሱ ነገር ገጥሞት እንደውሳ፡፡ አትፍረድ፤ ይፈረድብሃል፡፡ ደግሞ ኦሾ ምን ብሏል
መሰለህ፤ ‘ፍቅር እምቢ ካለህ በአልማዝ ቀለበት ምጣበት፤ ልኩን ያገኛል!’››
‹‹ኦሾ እንዲህ አለ እንዴ በናትህ?›› አለ እዬሳቀ፡፡
‹‹ሳይል አይቀርም ብዬ ነው፡፡ መቼስ ኦሾ የማይለው ነገር የለ!››
‹‹እየቀለድክ ነው መሰለኝ፡፡ …….አናዳጁ ነገር ደግሞ ምን መሰለህ?››
‹‹ምንድን ነው?››
‹‹ከጠቅልል ሚኒስትራችን ጋር እኮ ነው ተዛምዶት ያረፈው?!›› አለ ድምፁን ቀነስ አድርጎ፡፡
‹‹እኮ ቴዲ አፍሮ?›› አልኩ ጮክ ብዬ፤ ክፍት አፍ የሆንኩ ልጅ፡፡ እንዳው ምን ይሻለኛል?!
‹‹ታዲያስ!››
‹‹በተሰቀለው! በየት በኩል ባክህ?››
‹‹በናታቸው በኩል ነው አሉ!››
‹‹ሆ ሆ…..ይሄ ነገር እንዴት ነው፡፡ የቀጣዩ አልበም መጠሪያ  ‘ህዳሴው’  የሚል ይሆናል በለኛ!››
‹‹’ብሄር ብሄረሰብ’ ሊባልም ይችላል፡፡ እንደ ሮያል ቤተሰቡ ስምምነት ነው!››
‹‹ወይ ነገር፡፡ እንደ ሰለሞን ተካልኝ ‘ቅንድቡ’ የሚል ነጠላ ለቆ ጉድ እንዳያሰማን እንጂ እባክህ!››
‹‹ያኔማ እስከ ቀይ ባህር ድረስ ነው የማሯሩጠው፡፡….››
‹‹ይሄን ሁሉ መረጃ ግን የት ነው የምታገኘው?›› ስል ጠዬኩ፡፡
‹‹ፌስ ቡክ ነዋ፡፡ ፌስቡክ አያመጣው የለ፡፡ ሰሞኑንማ ተወው፡፡ ፌስቡክህን በከፈትክ ቁጥር ቴዲ አፍሮ ቆሞ፤ እጩ
ባለቤቱ ተቀምጣ፤ በግራ፣ በቀኝ፣ በኋላ፣ በፊት፣ በታች፣ በላይ፤ ወዘተ… ሲሳሳሙ ታያለህ፡፡ ይሄ እውነት ቴዲ
ካሳሁን ነው? ብለህ ልትጠራጠር ሲያምርህ ያቺን ውብ ፈገግታ ብልጭ አድርጎ ‘’አትጠራጠር እኔ ነኝ’’ ይልሃል
ቴዲዬ፡፡ ወይ ጉድ ብለህ ወይም ቀንተህ ወይም በጉምጃት ምራቅህን እንዳትጨርስ ሰግተህ ፌስ ቡክህን ትቆልፍና
ኢሜልህን ስትከፍት የማታውቀው ሰው ሰበር ዜና ብሎ ‘’ቴዲ አፍሮ ቀለበት አሰረ’’ ይሉት ሰባራ ዜና ይልክልሃል፡፡
ምርር ብሎህ ኤሜልህንም ፌስቡክህንም ጠርቅመህ ኖትቡክህን ገልጠህ እውቀት ለመመርመር ቁጭ ባልክበት ስራ ያጣው ቴሌ
የማይመለከትህን ሜሴጅ ይሰድልሃል፤ ብረትን ወርቅ የሚያደርጉ ወርቅ የሆኑ አልኬሚስት ዘመዶቻችን የመሰረቱት ሙዚቃችን
ሊያሳድግ ሊመነድግ የተነሳው አዲሱ የቢዝነስ ሞኖፖሊ የቴዲ አፍሮን ዘፈን ግዛ ይልሃል፡፡ መፅሃፍ ግዛ አይልህም
እኮ፤ መፅሃፍ ከገዛህማ ትበልጠዋለሃ፤ ካርል ማርክስን እየጠቀስክ ሞኖፖሊውን ድባቅ ትመታበታለሃ፤ ስለዚህ በዘፈን
ሊያዘናጋህ ይፈልጋል፤…..›› አለ በምሬት፡፡
‹‹አዲሱ ካፒታሊስት ሙዚቃችን ሊያሳድግ ቢነሳ አታሽሟጠው!›› አልኩት፡፡
‹‹አሁን ገና ልበልጥህ ነው፡፡ ልብህ ሳታድግ፤ ሳንባህ መጠኑ ቢጨምር የካንሰር ተጠቂ ትሆናለህ፡፡ በጣም እርቦህ
ሙዚቃ ሰምተህ ታውቃለህ? ረሃብህ እጥፍ ይጨምራል፡፡ የአገሬ ዘፈን አድጎ የአገሬ ህዝብ በአስተሳሰቡ በቆመበት
የሚረግጥ ከሆነ ማህበራዊ ካንሰር ተከሰተ ይባላል፡፡ ቴዲ አፍሮ ሚስት በማጨቱ አንዳንድ የአገሬ ሴቶች በብስጭት
በረኪና ካልጨለጥን ካሉ ካንሰር ማለት ይሄ ነው፡፡..…›› ሲል መለሰ፡፡
‹‹በጣም የመረረህ ትመስላለህ?›› አልኩት፡፡
‹‹እንኳን እኔ የፌስቡክ መስራች ማርክ ዙከርበርግ ራሱ ሳይመረው አልቀረም!››
‹‹እንዴት? ደሞ እሱ ምኑ ተነካና?››
‹‹የመሃመድ ቦአዚዝ አብዮት በአረቡ አለም፤ የቴዲ አፍሮና የእጮኛው ፎቶ ሾፕ በአበሻ አለም ፌስቡኩን
ሲያጨናንቁበትሳ!?›› ሲል መለሰ፡፡ እዚህ ላይ ጦሽ ብዬ ነበር የሳኩት፡፡
‹‹ለማንኛውም የአብርሃምና የሳራ ጋብቻ እንዲሆንለት ልመኝ መሰል!›› ሲል ቀጠለ፡፡
‹‹የፀጋዬ እና ፊያሜታን ፍቅር ያድርግለት ማለት አይሻልም?!››
‹‹ፀጋዬና ፊያሜታ እነማ ናቸው ልልህ ነበርኮ፡፡ ኦሮማይን ማንበቤ ትዝ አለኝ፡፡ በነገርህ ላይ የቴዲ አፍሮ ጥምረት
እኔን ጨምሮ የበርካታ ወንዶችን የሞራል ጥያቄ የመለሰ በመሆኑ በአንድ በኩል ይደነቃል!›› አለ፡፡
‹‹እንዴት?››
‹‹እንደምታዬኝ አጭር ነኝ፡፡ ረጂም ሴት አግብቼ ነበር፤ ኋላም ፈታቺኝ፡፡ የሰፈር ሰው ባለፍን ባገደምን ቁጥር
‘ፈረስና ባልደራስ’ እያለ በሽሙጥ ፍቅራችን ደመሰሰው፡፡ ረጂም ሴት ላላገባ ማልኩ፡፡ ረጂም ሴት ለማግባት አጭር
ወንዶች የሚፈሩት ለምን እንደሆነም ገባኝ፡፡ በዚህ በኩል ቴዲ አፍሮ የቁመት ባልደረቦቹን ነፃ ሳያወጣን
አልቀረም!›› አለ፡፡
‹‹ሴቶችኮ ወርቅ ልብ ማዬት ካልቻሉ ወርቅ ማዕድን፤ ወርቅ ማዕድን ማዬት ካልቻሉ ወርቅ ልብ ያያሉ እንጂ ቁመት
አያዩም፡፡ ሚስትህ የፈታችህ በሰፈር ሽሙጥ በቀላሉ የሚታጠፍ ሽቦ ልብህን አይታ እንጂ በቁመትህ ማጠር
አይመስለኝም!›› አልኩት፡፡
ደስ አለው፡፡ ተንደርድሮ መጥቶ ግንባሬን ሳመኝ፡፡
‹‹ከአመታት በፊት በቦክስ ልትተረትረው የነበረውን ግንባር አሁን ስትስመው ምን ተሰማህ›› አልኩት፡፡
‹‹ሃሴት ነዋ! ሃሴት!››
የጠጣሁትን ሻይ፤ የበላሁትን ኬክ ከፈለ፡፡ ‹‹ከሳምንት በኋላ ለውድድር ወደ ኦስሎ ኖሮዌይ እሄዳለሁ፡፡ ስመለስ
እደውልልሃለሁ!›› ብሎ ስልኬን ተቀበለ፡፡
‹‹ስንት ሺ ሜትር ነው የምትሮጠው?›› ስል ጠዬኩት፡፡
‹‹5 ሺ››
‹‹በል የቀነኒሳን ሪከርድ እንዳትሰብር ተጠንቀቅ!›› አልኩት:: (መቼስ የቀነኒሳ ነገር አይሆንልኝ፡፡ ቀነኒሳን
ሰሞኑን አይታችሁታል ወይ? ãረ ኦሎምፒክ ደርሷል ንቃ በሉት፡፡ ያያችሁት ካላችሁ አደራ ንገሩኝ፡፡ ናፍቆኛል፡፡
አቤት ስወደው፡፡ እዩኝ አይል፤ ስሙኝ አይል፤ ሳሙኝ አይል፤ ካልፈረምኩላችሁ አይል፤ ተደብቆ ከርሞ ይመጣና ሪከርድ
ሰብሮ ልማታዊ አርቲስት የሰበረውን ቅስማችን ይጠግንልናል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ አንዱ ሲሰብረው አንዱ እየደረሰ
ባይጠግነው ኖሮ ምን ይውጠው ነበር? ወገኔ ግን ሞኝ ነው፤ ከጠጋኙ ትቶ ከሰባሪው ጋር ይውላል፡፡ በሬ ካራጁ
እንደሚውለው፡፡)
‹‹ለምንድን ነው የቀነኒሳን ሪከርድ እንዳልሰብር የፈለከው?›› ብሎ ጠየቀ፡፡
‹‹ቀስ ብሎ ማደግ አይሻልም? ቶሎ ማደግ እኮ ነው አገር የፈታው፡፡ ቀርቀሃ ከወይራ ቀድሞ ያድግና በነፋስ ዝንጥፍ
ብሎ ይወድቃል!›› ብዬ መለስኩለት፡፡
ሳቀ፡፡
‹‹እንደ ቀነኒሳ አሸንፈህ አስፈንጥዘን በናትህ!›› አልኩት ቀጥሎ፡፡
‹‹አትጠራጠር፡፡ ይልቅ ስመለስ አበባ ይዘህ ኤርፖርት እንድትጠብቀኝ!›› አለ፡፡
‹‹ከቴዲ አፍሮ ጋር ማይክ ይዘን እንጠብቅሃለን፡፡ እኔ ለቃለመጠይቅ እሱ ሊዘፍንልህ!›› አልኩት፡፡
እየሳቀ ሄደ፡፡ ቀጥሬው የነበረው ጓደኛዬ ከርቀት ሲመጣ አየሁት፡፡ ከቀጠሮው ሰዓት በጣም ዘግይቶ ነበር፡፡ እንኳንም
ዘገዬ፡፡ እሱ ባይዘገይ ኖሮ ይሄ ወሬ ባልተፃፈ ነበር፡፡

የአባይ ውሐ አጠቃቀም የፖለቲካ ውዝግብ

ኢትዮጵያ እጎአ በ2010 ከላይኛው የአባይ ተፋሰሰ ሃገራት ማለትም ከብሩንዲ ከኬንያ ከሩዋንዳ ከታንዛንያ እና ከዩጋንዳ ጋር የአባይ ውሐን በጋራ መጠቀም የሚያስችለውን የኢንቴቤውን ስምምነት ከፈረመች ወዲህ የአባይ ወሐ ፖለቲካ አቅጣጫ መቀየሩ ተገልጿል ።

ኢትዮጵያ ና በግብፅ መካከል በአባይ ውሐ አጠቃቀም ሰበብ በየጊዜው የሚነሳው ውዝግብ ወዴት ሊያመራ ይችላል በሚለው ነጥብ ላይ ያተኮረ ውይይት በዚህ ሳምንት አጋማሽ በርሊን ውስጥ ተካሂዶ ነበር ። በውይይቱ ላይ  ኢትዮጵያ እጎአ በ2010 ከላይኛው የአባይ ተፋሰሰ ሃገራት ማለትም ከብሩንዲ ከኬንያ ከሩዋንዳ ከታንዛንያ እና ከዩጋንዳ ጋር የአባይ ውሐን በጋራ መጠቀም የሚያስችለውን የኢንቴቤውን ስምምነት ከፈረመች ወዲህ የአባይ ወሐ ፖለቲካ  አቅጣጫ መቀየሩ ተገልጿል ።  ይህ በአንድ በኩል የአካባቢው ሃገራት የሚያስተባብር ቢሆንም በዘዴ ካልተያዘ ግን አደጋም እንዳለው ተወያዮቹ ማስገንዘባቸውን የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ዘግቧል ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
 

ዓርብ 5 ኤፕሪል 2013

ሞተበት ሲላጭ፤ ያልሞተበት ቅቤ ይቀባል (የጉራጌ ተረት)


ከዕለታት አንድ ቀን የዱር አራዊት ከአንድ ውጊያ ድል በኋላ፤ እስቲ ያሳለፍነውን ጦርነት እንዴት እንዳሸነፍ
እንመርምር ይባባላሉ፡፡
ነብር - “የእኔ መኖር ነው ዋናው፡፡ የእኔ ፍጥነት ጠላቶቻቸውን አደነጋግሩዋቸዋል” አለ፡፡
ዝሆን - “የእኔ ግዙፍነት ጠላቶቻችንን ብርክ አሲዞዋቸው እንደነበር ሁላችሁም ምስክር ናችሁ” አለ፡፡
ዝንጀሮ - “እኔ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት በየዛፉ ላይ እየተንጠላጠልኩ ‘ወዮላችሁ! የአያ አንበሶ ጦር ዶጋመድ
ሊያደርጋችሁ እየመጣ ነው’ ስላቸው ጫካውን እየለቀቁ ሲፈረጥጡ አይታችኋል፡፡ ‘ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው’
የሚባለው ዕውነት መሆኑን ታዝባችኋል፤” አለ፡፡
አጋዘን - “እኔ በስንቅ፣ በትጥቅና በንብረት ጥበቃ ማገልገሌን መቼም አትክዱም፡፡ ዞሮ ዞሮ ዋናው ሁላችንም
የአያ አንበሶ ምልምሎች መሆናችን ነው፡፡ ያ መቼም አሌ አይባልም፡፡ ሁላችንንም የረዳን የሳቸው አቅምና ዝና ነው፡
፡ ድሉም የእሳቸው ውጤት ነው” አለና ተቀመጠ፡፡
ሁሉም በተራ በተራ ዘራፍ እያሉ ራሳቸውን እያደነቁ ተቀመጡ፡፡
በመጨረሻ ጦጢት ተነስታ፤
“እኔ ግን በመጠኑ ቅር ብሎኛል” አለች
“ለምን? ምክንያትሽን አስረጂና?” ተባለች፡፡
ጦጢትም እንዴት ስሜቷን ተቆጣጥራ እንደምትናገር በማስላት፤ ድምፁዋን አጠራችና፤
“ጌቶቼ! ወንድሞቼ! እህቶቼ! ጠላቶቻችንን በወኔ መደምሰሳችን እርግጥ ነው እጅግ አስደሳች ነገር ነው፡፡ ዕድሜ
ለጀግናው መሪያችን፤ በማያወላውል ሁኔታ ድል መትተናቸዋል!! የሚቀጥለውንም ውጊያ እንደምናሸንፍ ምንም
ጥርጥር የለኝም፡፡ ሆኖም ከእኛ ጋር ሊሆኑ የሚችሉትን ሁሉ ከጠላት ጋር ደርበን ማጥፋት ያለወገን ያስቀረናል፤
ብዬ እገምታለሁ፡፡ እና እንደምታውቁት በሌሎች ደኖች ደግሞ እኛን ለማጥቃት ጊዜ የሚጠብቁ በርካቶች እንዳሉ
እናውቃለን፡፡ ዓለም ተገለባባጭ ነው፡፡ አሮጌው ይሄድና አዲሱ ይተካል፡፡ እኛ ሄደን ተተኪው ይመጣል፡፡ ስለዚህ
እንዳለፈው ጊዜ ስለጦርነቱ እንኳ የሚያወራ አንድ አውሬ ሳናስቀር ሁሉንም መደምሰሱ፣ ነገ ይህን ጫካ ለቅቀን
ስንሄድ ወሬ ነጋሪ እንኳ እንዳይቀር ያደርጋል፡፡ ከጠላትም ለዓይነት አንዳንድ ብናስተርፍ ይሻላል፡፡ ደሞም እንደኛ
ሊያስብ የሚችለውን ብንለይና አብረን ብንጓዝ ጥሩ ነው”፡፡
ሁሉም “ጦጢት ውነቷን ነው” አሉ፡፡
***
ሁሉንም ጠራርጌ አጥፍቼ እኔ ብቻ ልቅር ማለት ጐጂ እንደሆነ እናስተውል፡፡ ሁሉን እንደመስሳለን፤ ሁሉን
ድባቅ እንመታለን ያሉ ከሂትለር እስከ ፒኖቼ Apre moi le deluge (እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል) ካለው የፈረንሳዩ
ሉዊ፤ ከቦልሼቪክ ደበኞች፣ በሴራ ተተኪ ነን እስካሉት እስከ “ጋንግ ኦፍ ፎር” በየዘመኑ ገነው ሲጠፉ አይተናል፡፡
ማንም ፊቴ አይቆምም የሚለው የሞንጐሊያዊው ጄንጂስ ካን ታሪክ መልካም ምሳሌ ይሆነናል፡፡
ሞንጐሊያውያን ቻይናን በወረሩ ሰዓት፤ ጄንጂስ ካን የተባለው መሪያቸው አሸንፎ ቻይና ሲገባ፣ ይቺ አገር
ለምንም አትሆንም ብሎ ከማሰብ ተነስቶ “ለፈረሴ እንኳን ለግጦሽ መሬት የሌላት አገር ናት ቻይና፡፡ ድምጥማጧን
ማጥፋት አለብኝ” አለ፡፡ “ለምን ታጠፋታለህ?” ሲባል፤
“እነዚህን ቻይናውያን ከምድረ - ገጽ አጥፍቼ መሬታቸው ላይ ለፈረሴ የግጦሽ ሣር ባበቅል ይሻላል” አለ፡፡ ይሄኔ
አንድ ቹ ሴይ የሚባል ብልህ ሰው፤ እንደምንም ተጣጥሮ የጄንጂስ ካን አማካሪ ሆኖ ነበርና፤ “ቻይናን ከምታጠፋት
እያንዳንዱ ቻይናዊ ቀረጥ እንዲከፍል ብታደርግ ብዙ ገንዘብ ልታገኝ ትችላለህ” አለው፡፡ ጄንጂስ ካን በምክሩ
ተስማማ፡፡ ቀጥሎ ግን አንዲት ካይ ፌንግ የምትባል ከተማ ወርሮ ሊያወድም ፈለገ፡፡ አማካሪው ቹ ሴይ፤ “ጄንጂስ
ካን ሆይ! የቻይና ጠበብት ሁሉ መሀንዲሶቹ፣ ሐኪሞቹ፣ ባለ እጆቹ … ሌሎች ከተሞቻቸው ሲወረሩ የመጡት
ወደዚች ከተማ ነው፡፡ ከተማይቱን ከማጥፋት ለምን በባለሙያዎቹ አትጠቀምባቸውም” ሲል መከረው፡፡ ጄንጂስ
ካን ምክሩን ተቀበለ፡፡ መንገዶች ተሠሩ፡፡ ህንፃዎች ተገነቡ፡፡ ሆስፒታሎች ተቋቋሙ፡፡
“ሰዎችን የሚነዳቸው የግል ፍላጐት ነው፡፡ ይህንን ፍላጐት ለማሳካት የሚያረጉትን ጥረት በማየትና በዘዴ
በማግባባት አገር ልታድን ትችላለህ” ይላል ቹ ሴይ፡፡
ችግሩ የሚመጣው ምክር የማይሰሙ መሪዎች ሲኖሩ ነው፡፡ ወይም ደግሞ ሰው ቀረጥ እንዲከፍል አድርግ
ሲባል በአንድ ጀንበር ሱሪ ባንገት አውልቅ ልበል ያለ እንደሆን ነው፡፡ የግል ፍላጐታቸው የአገር ካዝና የሚያራቁት
ከሆነ፣ ሙስናው ካጠጠና የዚህ መሸፈኛ ደግሞ “እኔ ብቻ ነኝ” የሚያስችል ሥልጣን ከሆነ አገር አለቀች፡፡
ከዚህ ቀደም ለዚች አገር ህልውና ሲባል መስዋዕትነት ተከፍሏል፡፡ ዛሬም ነገም ይከፈላል፡፡ መስዋዕትነቱ
የተከፈለው ተወዶ፣ ለውጥ በማምጣት ታምኖ፣ ከልብ ታግሎ ነበር፡፡
የተቀደሰ መስዋዕትነት የሚባለውም ያ ነው፡፡ አግባብ ነው፡፡ አግባብ የማይሆነው ተገዶ፣ ሳያስቡና ሳያልሙ፣
ምናልባትም ለምን እንደሆነ ሳያውቁ መስዋዕትነት መክፈል የሆነ እንደሆነ ነው፡፡ ህዝብ ማናቸውም ነገር ለምን
እንደሚከናወን የማወቅ፣ መረጃ የማግኘት መብት አለው፡፡ ያ ካልተከበረለት በገዛ አገሩ ባይተዋር፣ በገዛ ቤቱ እንግዳ
ይሆናል፡፡ “ሁሉም ነገር ለጽድቅ ነው - ዝም በል” ሲባል አሜን ካለ፤ የአቦ - ሰጡኝ መስዋዕትነት ከፈለ ማለት ነው፡፡
ለልጁ፣ ለትውልዱ የሚያስተላልፈው የመረጃ ቅርስ ሳይኖረው፣ በሕግ አምላክ የሚልበት ልሣን ሳይኖረው፣ አንዲት
የሰለጠነች አገር እየተመኘ ካለፈ፤ ለአገርም ለታሪክም ደግ አይሆንም፡፡
ጠንካራ ተቃዋሚ ስለሌለውም “ይሄ አይሆንም” ብሎ ሽንጡን ገትሮ፣ ታግሎ የሚያታግለው የለምና፣ ውሎ
አድሮ፤ ሁሉንም እየተካሄደ ያለውን ነገር “ይሁን ግዴለም ለበጐ ነው!” የሚልና “ለምን ይሆናል?” ብሎ የማይጠይቅ
ህዝብ ይፈጠራል፡፡ ይሄ አደጋ ነው! አንዱ ከአገር ጋር ሲያለቅስና አገር እንዴት ላድን ሲል፤ ሌለው አገር የሚገድል
ከሆነ፤ ገጣሚው
“..ዘመንና ዘመን እየተባረረ
ይሄው ጅምሩ አልቆ፣ ማለቂያው ጀመረ” እንዳለው ሊሆን ነው፡፡ የመተካካት ዘመን የራሱ አባዜ አለው፤ ሁሉም
እኩል ካልተሳሰበ ግን “የሞተበት ሲላጭ፣ ያልሞተበት ቅቤ ይቀባል” የሚለው የጉራጌ ተረት ዓይነት ይሆናል፡፡
ከዚያ ይሰውረን፡፡

ሐሙስ 4 ኤፕሪል 2013

ጥልያን በመድፍ በመትረየስ በአውሮፕላን ሊገድለው ያልቻለውን ጀግና በቅናት የተነሳሱ መቀኞች የሸረቡት ገመድ ገደለው


በላይ ዘለቀ ጀግና ብቻ አልነበረም፡፡ ባንዳነትን አድረባይነትን ሎሌነትን አጥብቆ ይጠላም እንደነበር ከዚህ ታሪኩ መረዳት እንችላለን፡፡ “….በላይ ዘለቀ ተኩሶ አይስትም ::ፍጥነቱ ደሞ ሲደግንና ሲተኩስ እኩል ነው ::ውጊያ ሊጀምር ሲል “እኔ ሳልተኩስ እንዳትተኩሱ ” ብሎ ያዛል ::አንዳንድ ጊዜ በውጊያ ሰአት “እርስዎ እዚህ ይቆዩን ” ሲሉት “ምን ?” ይላል ቁጣ እየጀመረው ::”እርስዎ ከወደቁ መሪ የለንም ” ሲሉት “ወይድ ! እኔ አሮጌ ነፍጠኛ ነኝ ::”ይልና ግንባር ይጋፈጣል :: በላይ ዘለቀ እራሱ ሲዋጋ “ገምባው ” ይተበባለው ጥሩንባው ይነፋል ::”ገምባው “ባንዳን ያስበረግጋል ::ጥልያንን ያብረከርካል ::
በላይ ዘለቀ የዘመኑን አስተሳሰብ በማወቁ ህዝቡን ለማስተባበር “ትልቅ ሰው ” ማስፈለጉን በመገንዘቡ እሱ እራሱ ግን ተራ ሰው በመሆኑ የንጉስ ተክለሀይማኖት ሀረግ ለሆኑት ለልጅ ሀይሉ በለው ደብዳቤ ጻፈላቸው :: የደብዳቤው ሀሳብ ባጭሩ “ህዝቡን ለማስተባበር እርስዎ የበላይ ሆነው እነን የጎበዝ አለቃ ይሹሙኝና ጠላትን እንቋቋመው ::እኔም እዋጋለሁ ::እርስዎ ወደጦር ግንባር መድረስ አይኖርብዎትም ::” የሚል ነበር ::ደጋግሞ ደብዳቤ ጻፈላቸው ::ገጸበረከትም ላከላቸው ::…ጠመንጃ ሽጉጥ ዝናር ከነጥይቱ ሶስት መቶ ብርና ካባ :: ልጅ ሀይሉ በለው ለደብዳቤዎቹ አንድም መልስ ሳይሰቱ አንድ ቀን አንድ የትእዛዝ ደብዳቤ ላኩበት ::”ደብረወርቅ ገበያችንን ያለአግባብ ቀረጡብን ብለዋልና ከንግዲህ ቆቅ የሰገረ ወፍ የበረረ እንዳይደርስባቸው ::የተወሰደባቸውም ቀረጥ እንዲመለስላቸው ::”
በላይ ዘለቀ ተናደደ ::አብረውት የነበሩትን “ጎበዝ እግዚአብሄር የወለደው ሰው አለ ?” ሲል ጠየቀ :: “እግዚአብሄር ይፈጥራል እንጂ አይወልድም ” አሉት :: “ንጉስስ ?” “ንጉስም እግዚአብሄር ይቀባዋል እንጂ አይወልድም ::ይፈጥረዋል እንደሌላሰው ” “እኔንም ፈጥሮኛል ::ሊቀባኝ አይችልም ?” “የሱ ሀይል ካደረብዎ የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ ::” “እንግዲህ ከዛሬ ጀምሮ ለማንም አልታጠቅም ::” ተመስገን ፈንታ የበላይ ዘለቀ የቅርብ ጉዋደኛው ነበር ::አንድ ቀን ከጠላት በፊት ተመስገን ፈንታ በላይ ዘለቀን “ሸዋ ሄደን ለትልቅ ሰው እንደር ::እንሾማለን ;እንሸለማለን “አለው :: “እኔ ሰው ሆኜ ለሰው አላድርም “አለ በላይ ዘለቀ :: “ባንተ ተኩስ ;ባንተ ወኔ ;ባንዳፍታ ትሾማለኽ :: “ጀግንነት እደጃችን ድረስ ይመጣ እንደሆነ ማን ያውቃል ?” አለው በላይ ዘለቀ ::አመታት አለፉ ::
ሞረድ እጀ ጠባብ ካስመራ እሚመጣ አፈ ሾሌ ሱሪና ተመሳሳይ ኮኮት ጥንግ ድርብ ጥበብ ኩታ በቅሎ እንደተጫነች ጠመንጃ ከነሙሉ ዝናር ጥይት …በላይ ዘለቀ ይህንን ሁሉ አዘጋጀና ተመስገን ፈንታን ጠርቶ ; “ያ የጌታ አዳር ሄደን እንሸለማለን ያልከው ይኸውና “ብሎ ሸለመው ::በአርበኝነት ዘመን ጉዋደኛሞቹ አልተለያዩም :: በላይ ዘለቀ መጀመርያ “ራስ ” ብሎ የሾመው ተመስገን ፈንታን ነበር :: “እኔንስ ራስ አልከኝ ::አንተ ማን ልትባል ነው ?” አለው ተመስገን ፈንታ :: “እኔንማ እናቴ አንደዜ በላይ ብላኛለች ” አለ በላይ ዘለቀ ::” ……….
የበላይ መጨረሻም ይህ ሆነ፡፡ ንጉስ ሹም ሽር አደረጉ ::በላይ ዘለቀ ከወንድሞቹ ጋር ሆኖ በሁዋላም ከአገሬው ጋር ሆኖ ጠላትን ተዋግቶ ነጻ ያወጣው ጠቅላይ ግዛት ለራስ ሀይሉ ተሰጠ :: በላይ ዘለቀ ወዳዲሳባ ተጠርቶ ደጃዝማች ተብሎ የቢቸና አውራጃ ገዥ ሆኖ ተሾመ :: የቢቸና አውራዣ ገዥ ሆኖም ሊሰራ አልቻለም ::ከደብረ ማርቆስ ትእዛዝ እየመጣ ወረዳዎቹ ሁሉ ቀድሞ ባንዳ የነበሩ ሰዎች ተሾሙባቸው ::ብስጭት በዛበት በላይ ዘለቀ :: “ሊወጋን ነው ….እምቢ አለ …”እያሉ ማስወራት ጀመሩ :: በቂ ካስወሩ በሁዋላ ከራያና አዘቦ ጦር አስዘመቱበት :: (ጎጃመማ በላይ ዘለቀን ወይ ይወደዋል ወይ ይፈራዋል :: ) በላይ ዘለቀና ወንድሞቹ ከጥቂት ታማኝ ተከታዮቹ ጋር ሆነው ወደ ሳማ አምባ ሸሹ ::በላይ ዘለቀ ሸፈተ ተባለ :: ሳማ አምባ ያለ ሁለት በር የላትም ሁለቱንም በር ይዘው ሀያ አምስት ቀን ሌትና ቀን ተዋጉ :: “ምረነዋል ልቀቁት ይምጣ “የሚል መልእክት ከንጉሱ መጣ :: ከሳማ አምባ ከወረዱ በሁዋላ ተከበቡና መሳሪያቸውን ተነጥቀው እንደ እስረኞች ወደ አዲስ አበባ ተወሰዱ :: በላይ ዘለቀ ሞት ተፈረደበት ::ንጉሱ “ምህረት ” አደረጉለትና ቅጣቱ ወደ እስራት ተለወጠለት ::
መስከረም 1936 አ .ም በላይ ዘለቀና ወንድሞቹ በያገሩ ተበትነው ታሰሩ :: በላይ ዘለቀና ወንድሙ እጅጉ ዘለቀ ወሊሶ በበቀለ ወያ ጠባቂነት ታሰሩ :: የበላይ ዘለቀ ምቀኖች አሁንም አላረፉለትም ::በላይ ዘለቀ ከዳ ;አመለጠ ጠፋ እየተባለ ይወራ ጀመር ::በቀለ ወያ ተያዘና “ምን ቢሰጥህ ነው የለቀከው ?”ተባለ ::”እረ እኔ አልለቀኩትም አለ :::: በላይ ዘለቀና እጅጉ ዘለቀን ወደ አዲስ አበባ አመጡዋቸውና ከአንድ ሌላ ሰው ጋር አሰሩዋቸው :.ያ ሰው እናምልጥ እያለ እነ በላይ ዘለቀን ይጎተጉታቸው ጀመር :: አንድ ቀን “ጠባቂዎቻችንን የኛ ወዳጆች ገዝተዋቸዋልና እናምልጥ ::በንዲህ ያለ ስፍራ እነ እገሌ መኪና ይዘው እየጠበቁን ናቸው ::”አል :: “ወንድሞቸ በየቦታው ተበታትነው ታስረው እኔ ማምለጥ ምን ያረግልኛል ?” አለ በላይ ዘለቀ :: “ፈራህ እንዴ በላይ ዘለቀ ?”አለው :: “እኔ የዘለቀ ልጅ !” በላይ ዘለቀ ወንድሙን ላከው መኪናው እተባለበት ስፍራ መኖሩን ለማረጋገጥ ::ወንድምየው በተባለበት ስፍራ መኪና አየ ::እስረኞቹና ጠባቂዎቻቸው አብረው አመለጡ ::እመኪናው ቦታ ሲደርሱ መኪናው የለም ::እንግሊዝም የለም :: ጠባቂዎቻቸው ከዚያ ሮጠው አጠገባቸው ከነበረው ጫካ ገቡና ደጋግመው ተኮሱ ::ምልክት ነው :: በላይ ዘለቀ እጠላቶቹ ወጥመድ ውስጥ መግባቱን አወቀ :: በላይ ዘለቀና እጅጉ ዘለቀ ከዚያ እሮጠው አመለጡ :: ሰላሌ ደርሰው በቅሎ ለመከራየት ሲነጋገሩ ተከበቡ :: በላይ ዘለቀ በጦር ፍርድ ቤት ሞት ተፈረደበት ::ንጉሱ ፍርዱን አጸደቁት :: ጥር 1937:.በላይ ዘለቀ በስቅላት ሞተ ::እድሜው ሰላሳ አምስት አመት ነበር ::
ጥልያንን በመድፍ በመትረየስ በአውሮፕላን ሊገድለው ያልቻለውን ጀግና በቅናት የተነሳሱ መቀኞች የሸረቡት ገመድ ገደለው ::ፊታውራሪ ተሻለ አለሙ ሰላሳ አምስት አመት ታስረው በለውጡ ተፈቱ::መልኩን ፊታውራሪ ተሻለ አለሙ እንዲህ ብለው ይገልሱታል :: “አፍንጫው ሰተት ብሎ ወርዶ ቅጠሉ ነፋ ነፋ ይላል ::ከንፈሩ ከበድ ይላል ::ጠጉሩ ክርክም ጎፈሬ ጺሙ ሙሉ ለስላሳ ረጅም ጣቱ መልካም ወተት የተነከረ ነው የሚመስለው ጣቱ ::እግረ ቀጭን ::”…………..”
ዛሬም እንደዚህ ነው…. ስንት አድርባዮችና አሰመሳዮች አለን? ኑሮአችንን በሌሎች ህልውና ላይ የመሰረትን? የአፋኝ ሥርዐት ሎሌ በመሆን የወንድሞቻችንን ደም ከንቱ ያደረግን…..? 
posted by Mulle
By LAAA-LIQE MOTSA